ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት።
ዘኍል 31:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁንና በልዩ ልዩ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ከእጃቸው ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ የተሠራውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ከእነርሱ ወርቁንና በልዩ ልዩ ቅርፅ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴና አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ ተሠርቶ የነበረውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁንና በልዩ ልዩ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ከእጃቸው ተቀበሉ። |
ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት።
ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ለእግዚአብሔር የለዩትና ያቀረቡት ወርቅ ሁሉ ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ሰቅል ነበረ።