ዘኍል 31:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምርኮውንም በተዋጉትና ወደ ሰልፍ በወጡት፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል ትከፍላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምርኮውንም ለሁለት ከፍላችሁ በጦርነቱ ለተካፈሉት ወታደሮችና ለቀረው ማኅበረ ሰብ አከፋፍሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምርኮውንም ወደ ጦርት ወጥተው በተዋጉትና፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል ለሁለት ክፈል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለት መድባችሁም አንደኛውን ክፍል ወደ ጦርነት ለሄዱ ወታደሮች፥ ሁለተኛውን ክፍል ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ስጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምርኮውንም በተዋጉትና ወደ ሰልፍ በወጡት፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል አስተካክለህ ክፈል። |
እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ።
“በብዙ ብልጥግና፥ በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”