ዘኍል 30:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቷም ስእለቷንና ራስዋን የለየችበትን ቢሰማ፥ አባቷም ዝም ቢላት፥ ስእለቷ ሁሉ ይጸናል፤ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቷም መሳሏን ወይም ራሷን ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሰምቶ ምንም ነገር ሳይላት ቢቀር፣ ስእለቶቿ በሙሉ፣ ራሷንም ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች ሁሉ መፈጸም ይኖርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትዋ ስለዚህ ጉዳይ ሰምቶ ካልተቃወማት በቀር ስእለትዋን ወይም የገባችውን ቃል መፈጸም አለባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል። |
አባቷ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ ስእለቷ፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላዋ አይጸኑም፤ አባቷ ከልክሎአታልና እግዚአብሔር ይቅር ይላታል።