ዘኍል 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ድንኳኑ ሥራዎች ሁሉ የምስክሩን ድንኳን ዕቃና የእስራኤልን ልጆች ሕግ ይጠብቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማደሪያውን ሥራ በመሥራትና የእስራኤላውያንን ግዴታ በመወጣት የመገናኛውን ድንኳን ሁሉ ይጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማደሪያውንም ሥራ እየሠሩ፥ የመገናኛውን ድንኳን ዕቃ ሁሉ ይጠብቃሉ፥ ለእስራኤልንም ልጆች ያለባቸውን ግዴታ ይወጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚገኙ መገልገያ ዕቃዎች ኀላፊዎች ይሆናሉ። እስራኤላውያንንም በድንኳኑ ውስጥ በማገልገል ተግባራቸውን ይፈጽማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማደሪያውንም ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የመገናኛውን ድንኳን ዕቃ ሁሉ ይጠብቁ፥ የእስራኤልን ልጆች ለማገልገል የሚያስፈልገውንም ነገር ይጠብቁ። |
አሁንም በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
ሌዋውያንንም ወደ ወንድምህ ወደ አሮንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህናቱ ታገባቸዋለህ። ከእስራኤል ልጆች ተለይተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰጥተዋልና።
ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይገባሉ። እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በምስክሩ ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።
በምስክሩ ድንኳን ዘንድ ባለው ሥራቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው፤ እነርሱም ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች ይሆናሉ።”