በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
ዘኍል 29:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን ከመጠጡም ቁርባን ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት ደግሞ አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት የእህል ቊርባንና የመጠጥ ቊርባን ሌላ በተጨማሪ ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው። |
በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
የእህል ቍርባናቸውና የመጠጥ ቍርባናቸው ለበሬው፥ ለአውራውም በግ፥ ለጠቦቶቹም እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጋቸው ይሆናሉ።
“እነዚህንም፥ ከስእለታችሁና በፈቃዳችሁ ከምታመጡት ሌላ፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእህልም፥ ለመጠጥም ቍርባን፥ ለደኅንነትም መሥዋዕታችሁ በበዓላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።”