በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በበዓላትም ለሚቀርበው ለሚቃጠለው መሥዋዕት ንጉሡ ከገንዘቡ የሚከፍለውን ወሰነ።
ዘኍል 29:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በስድስተኛውም ቀን ስምንት በሬዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በስድስተኛውም ቀን ስምንት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በስድስተኛው ቀን ነውር የሌለባቸውን ስምንት ኰርማዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስድስተኛውም ቀን ስምንት ወይፈኖች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ነውር የሌለባቸውን አሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ |
በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ተጻፈ በጥዋትና በማታ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በበዓላትም ለሚቀርበው ለሚቃጠለው መሥዋዕት ንጉሡ ከገንዘቡ የሚከፍለውን ወሰነ።
በየበዓላቱም፥ በየመባቻውም፥ በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን መስጠት በአለቃው ላይ ይሆናል፤ እርሱ ለእስራኤል ቤት ያስተሰርይ ዘንድ የኀጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርባል።”
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።
ለበሬዎችና ለአውራ በጎቹ፥ ለጠቦቶቹም የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን እንደ ቍጥራቸው መጠን እንደ ሕጋቸው፥