ዘኍል 26:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያም ልጆች በየወገናቸው፤ ከበዓሌ የበዓላውያን ወገን፥ ከአሲቤር የአሲቤራውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች። እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የዳን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሰምዔ የሰምዔያውያን ወገን፤ በየወገናቸው የዳን ወገኖች እነዚህ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳን ነገድ ተወላጆች ሰሜዔና፤ ተወላጆቹ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየወገናቸው የዳን ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሰምዔ የሰምዔያውያን ወገን፤ በየወገናቸው የዳን ወገኖች እነዚህ ናቸው። |
የዳን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደእየ ስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
እነዚህ የኤፍሬም ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው።