ዘኍል 26:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም የምናሴ ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት አምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብንያም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በቤላ በኩል፣ የቤላውያን ጐሣ፣ በአስቤል በኩል፣ የአስቤላውያን ጐሣ፣ በአኪራን በኩል፣ የአኪራናውያን ጐሣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገናቸው የብንያም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከቤላ የቤላውያን ወገን፥ ከአስቤል የአስቤላውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ነገድ በየትውልዳቸው ቤላ፥ አሽቤል፥ አሒራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያም ልጆች በየወገናቸው፤ ከቤላ የቤላውያን ወገን፥ ከአስቤል የአስቤላውያን ወገን፥ ከአኪራን የአኪራናውያን ወገን፥ ከሶፋን የሶፋናውያን ወገን፥ |
የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስቤር፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ኖሔማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራድን ወለደ።
የጋድ ልጆች በየትውልዳቸው- በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
የኦፌርም ልጅ ሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የሰለጰዓድም የሴቶች ልጆቹ ስም መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበረ።
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።