ዘኍል 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቢዖር የጥፋት ጎጆ ቢሆንም አሦር ይማርክሃል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ሆኖ ግን እናንተ ቄናውያን፤ አሦር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቄናዊው ግን ለጥፋት የተዘጋጀ ይሆናል። አሦር የሚማርክህ እስከ መቼ ድረስ ይሆን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ቄናውያን፥ አሦር ድል ነሥታ በምትማርካችሁ ጊዜ ትደመሰሳላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አሦር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊው ለጥፋት ይሆናል። |
ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች ቤቶች አለቆችም ቀርበው፥ “የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለአምላካችሁ እንሠዋለንና፥ እንደ እናንተም እንፈልገዋለንና ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው።
ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን።
አግንም ባየው ጊዜ በምሳሌ ይናገር ጀመር፤ እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ አወይ ማን በሕይወት ይኖራል?