ዘኍል 23:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን አለው፥ “ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ትረግምልኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይወድድ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ባላቅ በለዓምን፣ “በል እንግዲያው ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ፤ ከዚያ ሆነህ እንድትረግምልኝ ምናልባት እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ብትረግምልኝ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅም “ና ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ ምናልባት ከዚያ ሆነህ ይህን ሕዝብ እንድትረግምልኝ እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በለዓምን፦ ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ትረግምልኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይወድዳል አለው። |
ቅዱስ እግዚአብሔር ይህን መክሮአል፤ የእግዚአብሔርን ምክር የሚመልስ ማን ነው? የተዘረጋች እጁንስ የሚመልሳት ማን ነው?
እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፈነ፤ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል፤ አሁንም ይህ ሕዝብ ከእኔ ይበልጣልና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደ ሆነ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የመረቅኸው ምሩቅ፥ የረገምኸውም ርጉም እንደ ሆነ አውቃለሁና” ብሎ ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ።
ባላቅም፥ “በዚያ እነርሱን ወደማታይበት ወደ ሌላ ቦታ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ና፤ ከእነርሱ አንዱን ወገን ብቻ ታያለህ፤ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም እነርሱን ርገምልኝ” አለው።