ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
ዘኍል 22:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በአህያዪቱ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ሁለቱም ብላቴናዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ። አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመንገዱም ላይ ፈቀቅ ብላ ወደ ሜዳ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ ይመልሳት ዘንድ አህያዪቱን መታት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አህያዪቱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ በመንገድ ላይ መቆሙን ባየች ጊዜ ከመንገድ ወጥታ ዕርሻ ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገዱ እንድትመለስ መታት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አህያይቱም የጌታን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ እርሷም ከመንገዱ ፈቀቅ ብላ ወደ እርሻው ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ እንድትመለስ አህያይቱን መታት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩ ሰይፉን መዞ በመንገዱ ላይ መቆሙን አህያይቱ በተመለከተች ጊዜ መንገዱን ለቃ ወደ እርሻ ገባች፤ በለዓምም አህያይቱን ወደ መንገዱ ለመመለስ ደበደባት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየች፤ ከመንገዱም ፈቀቅ ብላ ወደ እርሻው ውስጥ ገባች፤ በለዓምም ወደ መንገድ ይመልሳት ዘንድ አህያይቱን መታት። |
ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትና ሽማግሌዎቹም ማቅ ለብሰው በግንባራቸው ተደፉ።
ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ፥ ዋሊያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?” አለው።