ዘኍል 21:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የምሳሌ ሰዎች እንዲህ ብለው ይናገራሉ፦ “ወደ ሐሴቦን ኑ፤ የሴዎን ከተማ ይመሥረት፤ ይገንባ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ባለቅኔዎች እንደዚህ ያሉት ለዚህ ነው፤ “ወደ ሐሴቦን ኑ፣ እንደ ገና ትገንባ፤ የሴዎንም ከተማ ተመልሳ ትሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ባለቅኔዎች እንዲህ ብለው በምሳሌ ተቀኙ፦ “ወደ ሐሴቦን ኑ። የሴዎን ከተማ ይሠራ፥ ይመሥረትም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ ባለቅኔዎች እንኳ እንዲህ እያሉ ይቀኙ ነበር፦ “ወደ ሐሴቦን ኑ! ይህች ከተማ ትገንባ! የሲሖን ከተማ ትመሥረት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በምሳሌ እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ ወደ ሐሴቦን ኑ። የሴዎን ከተማ ይሠራ፥ ይመሥረት፤ |
ይህንም ሙሾ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፤ እንዲህም ትላለህ፥ “አስጨናቂ እንዴት ዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!
እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?
ሐሴቦንም የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረ፤ እርሱም የፊተኛውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ ከአሮኤር እስከ አርኖን ድረስ ምድሩን ሁሉ ወስዶ ነበር።