ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።
ዘኍል 21:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድርህ ላይ እንለፍ፤ በመንገዱም እንሄዳለን፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጕድጓድህም ውኃን አንጠጣም፤ እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጎዳና እንሄዳለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አገርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን፤ ወደ የትኛውም ዕርሻ ሆነ የወይን አትክልት አንገባም፤ ወይም ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስም የንጉሡን አውራ ጐዳና አንለቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድርህ ላይ ልለፍ፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጉድጓድም ውኃን አንጠጣም፤ ግዛትህን አልፈን እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድርህ አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ እኛና ከብቶቻችን ከመንገዱ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም ውሃ አንጠጣም፤ ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስ ዋናውን መንገድ አንለቅም።” |
ወደ እግዚአብሔርም ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፤ መልአክንም ልኮ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።
እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፤ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጎዳና እንሄዳለን፤ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”