ዘኍል 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በመጽሐፍ ተባለ የእግዚአብሔር ጦርነት ዞኦብንና የአርኖን ሸለቆዎችን አቃጠለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በዚሁ የተነሣ ነው፤ “…በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ አርኖንና መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በጌታ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ “ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር መሪነት ስለ ተደረገው ጦርነት በሚናገር የታሪክ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎአል፦ “በሱፋ ክልልና በሸለቆዎች ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ፥ የአርኖን ወንዝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥ |
ከዚያም ተጕዘው ከአሞራውያን ዳርቻ በሚወጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።
ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፤ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ፥ አሞሬዎናዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን፥ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርስዋን ግዛት፤ ውረሳት፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።
እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን እስኪያጠፋ ድረስ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽሐፍ በጊዜው ተጻፈ። ፀሐይም በሰማይ መካከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አልጠለቀችም።
ሳኦልም ዳዊትን፥ “ታላቂቱ ልጄ ሜሮብ እነኋት፤ እርስዋን እድርልሃለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁንልኝ፤ ስለ እግዚአብሔርም ጦርነት ተጋደል” አለው። ሳኦልም፥ “የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእርሱ ላይ አትሁን” ይል ነበር።