La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 18:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም ከእ​ርሱ ባነ​ሣ​ችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ች​ሁም፤ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የቀ​ደ​ሱ​ትን አታ​ር​ክሱ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የተመረጠውን ክፍል ካቀረባችሁ በዚህ በደለኞች አትሆኑም፤ ደግሞም የተቀደሰውን የእስራኤላውያንን መባ አታረክሱም፤ አትሞቱምም።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የተመረጠውንም ከእርሱ ባቀረባችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤልን ልጆች የተቀደሱ ነገሮች አታረክሱም።’ ”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምርጥ የሆነውን ነገር ለእግዚአብሔር ካቀረባችሁ በኋላ በምትመገቡበት ጊዜ በደል አይኖርባችሁም፤ ነገር ግን ምርጥ የሆነው ነገር ከእርሱ ላይ ሳይነሣ ከስጦታው በመመገብ የእስራኤላውያንን የተቀደሰ ስጦታ እንዳታስነውሩ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተመረጠውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታረክሱም።

Ver Capítulo



ዘኍል 18:32
10 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ሁም ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ሞ​ቱም፥ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገቡ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሲቀ​ርቡ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ላይ ይሆ​ናል፤ ለእ​ርሱ፥ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።


የበ​ላ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አር​ክ​ሶ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ ከሚ​ቀ​ድ​ሱ​አ​ቸው ከቅ​ዱ​ሳን ነገ​ሮች ራሳ​ቸ​ውን እን​ዲ​ለዩ፥ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ስሜን እን​ዳ​ያ​ረ​ክሱ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ንገ​ራ​ቸው፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


በመሠዊያዬ ላይ ርኩስ እንጀራ ታቀርባላችሁ። እናንተም፦ ያረከስንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተነቀፈ ነው በማለታችሁ ነው።


ከዚ​ህም በኋላ ለሞት የሚ​ያ​በቃ በደል እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አይ​ግቡ።


እና​ን​ተም ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁም፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ የማ​ገ​ል​ገ​ላ​ችሁ ዋጋ ነውና በሁሉ ስፍራ ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


አሁ​ንም ሳይ​ገ​ባው ይህን ኅብ​ስት የበላ፥ ይህ​ንም ጽዋ የጠጣ የጌ​ታ​ችን ሥጋ​ውና ደሙ ስለ​ሆነ ዕዳ አለ​በት።


ሳይ​ገ​ባው፥ የጌ​ታ​ችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያ​ውቅ፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም ሳያ​ነጻ፥ የሚ​በ​ላና የሚ​ጠጣ ለራሱ ፍር​ዱ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ይበ​ላል፤ ይጠ​ጣ​ልም።