በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ዘኍል 18:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባችሁም እንደ እህል ዐውድማው ስንዴና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍርባናችሁም ከዐውድማ እንደ ገባ እህል ወይም ከመጭመቂያ እንደ ወጣ ወይን ሆኖ ይቈጠርላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ስጦታ የምታቀርቡት ቁርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ሙላት ይቈጠርላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ልዩ መባ አንድ ገበሬ ከአዲስ እህል ወይም የወይን ጠጅ ዐሥራት አውጥቶ እንደሚሰጠው ዐይነት ሆኖ ይቈጠርላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማንሣት ቍርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል። |
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለይታችሁ ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደምትለዩት ቍርባን እንዲሁ ትለያላችሁ።
“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ከእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን ዐሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ እናንተምከእርሱ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ የዐሥራት ዐሥራት ታቀርባላችሁ።
እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ የእግዚአብሔርንም መባ ለይታችሁ ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።
ስለዚህ ትላቸዋለህ፦ ከእርሱ ከመጀመሪያው በለያችሁ ጊዜ እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ለሌዋውያን ይቈጠርላቸዋል።
ነገር ግን ከበጎችህ፥ ከእህልህም፥ ከወይንህም መጭመቂያ ስንቅ ትሰንቅለታለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ።