Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እንደ ስጦታ የምታቀርቡት ቁርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ሙላት ይቈጠርላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ቍርባናችሁም ከዐውድማ እንደ ገባ እህል ወይም ከመጭመቂያ እንደ ወጣ ወይን ሆኖ ይቈጠርላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ይህም ልዩ መባ አንድ ገበሬ ከአዲስ እህል ወይም የወይን ጠጅ ዐሥራት አውጥቶ እንደሚሰጠው ዐይነት ሆኖ ይቈጠርላችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 መባ​ች​ሁም እንደ እህል ዐው​ድ​ማው ስን​ዴና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ይቈ​ጠ​ር​ላ​ች​ኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የማንሣት ቍርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ፍሬ ይቈጠርላችኋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 18:27
9 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ እነርሱን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ከእርሱ የተመረጠውን ባቀረባችሁ ጊዜ ከአውድማው እህልና ከወይን መጭመቂያው እንደ ተገኘ ምርት ለሌዋውያን ይቈጠራል።


ንጉሡም “እግዚአብሔር ሊረዳሽ ካልፈቀደ እኔ ምን ዓይነት እርዳታ ልሰጥሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይስ ከወይን መጭመቂያው? ምን ያለኝ ይመስልሻል?


ከመንጋህ፥ ከአውድማህና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው፤ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ።


መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ አንድ እንጐቻ ልዩ ስጦታ የሆነ ቁርባን አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደ ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ እንደምታቀርቡት ቁርባን እንዲሁ ታቀርቡታላችሁ።


በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ መጡ፥ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፥ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።


“ለሌዋውያን ተናገር እነርሱንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ለጌታ ለስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።


እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት አሥራት ሁሉ ለጌታ እንደ ስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን ታቀርባላችሁ፤ ከእርሱም የጌታን የስጦታ ቁርባን ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios