እነዚህም ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕቶች ለአንተና ለልጆችህ ሥርዐት እንዲሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመሥዋዕቱን ፍርምባና ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋርም ልጆችህ፥ ቤተሰብህም ተለይቶ በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ።
ዘኍል 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ለእናንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እስራኤላውያን ከሚያቀርቡት ስጦታ፣ ከሚወዘወዘው ቍርባን ተለይቶ የሚቀመጠው ስጦታ ሁሉ የአንተ ይሁን። ይህንም ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ። ከቤተ ሰዎችህ በሥርዐቱ መሠረት የነጻ ማንኛውም ሰው ከዚሁ መብላት ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ደግሞ ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ የሚያቀርቡትን የመወዝወዝ ቁርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በተጨማሪም እስራኤላውያን በእኔ ፊት በመወዝወዝ የሚያቀርቡአቸው ልዩ ስጦታዎች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ እነርሱን ለአንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻለሁ፤ ንጹሕ የሆነ ማንኛውም የቤተሰብህ አባል ሊመገባቸው ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀደሰ ይሆንልሃል። ይህም ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ ያቀረቡትን የማንሣትና የመወዝወዝ ቍርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። |
እነዚህም ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕቶች ለአንተና ለልጆችህ ሥርዐት እንዲሆኑ ስለ ተሰጡ፥ የመሥዋዕቱን ፍርምባና ወርች አንተ፥ ከአንተ ጋርም ልጆችህ፥ ቤተሰብህም ተለይቶ በንጹሕ ስፍራ ትበላላችሁ።
ከቍርባኑም ሁሉ የእግዚአብሔርን ድርሻ ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።
እግዚአብሔርም አሮንን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ወገኖች፥ የክህነታችሁን ኀጢአት ትሸከማላችሁ።
የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የሚለዩትን የተቀደሰውን መባ ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ሰጥቼሃለሁ፤ ይህም ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም ሕግና የሁልጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”
እግዚአብሔርም አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የለዩትን የመጀመሪያውን ቍርባኔን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተ እስክታረጅ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ።
በሬ ወይም በግ ለመሥዋዕት ከሚያቀርቡት ሕዝብ የካህናቱ ወግ ይህ ይሆናል፤ ወርቹንና ሁለቱን ጕንጮቹን፥ ጨጓራውንም ለካህኑ ይሰጣሉ።