በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
ዘኍል 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም በትሮቹን ወስዶ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ በእግዚአብሔር ፊት አኖራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በትሮቹን በጌታ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ወስዶ በድንኳኑ ውስጥ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ለፊት አኖራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። |
በካህኑ በአሮን ልጅ በይታምር እጅ የሌዋውያን ተልእኮ ይሆን ዘንድ ሙሴ ከእግዚአብሔር እንደታዘዘ የምስክሩ ድንኳን ሥርዐት ይህ ነው።
ነገር ግን በምስክሩ ድንኳንና በዕቃዎችዋ ሁሉ፥ በውስጥዋም ባለው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን አቁማቸው። ድንኳንዋንና ዕቃዎችዋን ሁሉ ይሸከሙ፤ ያገልግሉአትም፤ በድንኳንዋም ዙሪያ ይስፈሩ።
ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ላይ ዕዳ እንዳይሆንባቸው ሌዋውያን በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ ፊት ለፊት ይስፈሩ፤ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን ሕግ ይጠብቁ።”
ማኅበሩ ሁሉ ግን “በድንጋይ እንውገራቸው” አሉ። የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በምስክሩ ድንኳን ተገለጠ።
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤ አለቆቻቸውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች።
ደግሞም የአባትህን የሌዊን ነገድ ወንድሞችህን ወደ አንተ ሰብስብ፤ ከአንተም ጋር በአንድነት ይሁኑ፤ ያገልግሉህም፤ አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ትሆናላችሁ።
ድንኳንዋን በተከሉበት ቀን ደመናው የምስክሩን ድንኳን ሸፈናት፤ ከማታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በድንኳኑ ላይ እንደ እሳት ይመስል ነበር።