ዮቶርም ሙሴ በሕዝቡ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቶ እንዲህ አለው፥ “ብቻህን ተቀምጠህ በሕዝቡ የምታደርገው ይህ ምንድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመዋል።”
ዘኍል 15:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት እንደሚያደርጉት አልፈረዱምና በግዞት ቤት አዋሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰውየው ላይ ምን መደረግ እንዳለበት ግልጽ የሆነ ነገር ባለመኖሩ በጥበቃ ሥር እንዲቈይ አደረጉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱም ላይ ምን ሊደረግበት እንደሚገባ ገና ግልጽ አልነበረምና በእስር ቤት አኖሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ግልጥ ሆኖ ስላልተገኘ ለጊዜው በዘብ ተጠብቆ እንዲቈይ ተደረገ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያደርጉበትም ዘንድ የሚገባው አልተገለጠምና በግዞት አስቀመጡት። |
ዮቶርም ሙሴ በሕዝቡ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቶ እንዲህ አለው፥ “ብቻህን ተቀምጠህ በሕዝቡ የምታደርገው ይህ ምንድን ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመዋል።”