“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥
ዘኍል 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንድ ሰው ሳያውቅ ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢአት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ነገር ግን አንድ ሰው ካለማወቅ የተነሣ በግሉ ኀጢአት ቢሠራ ግን ለኀጢአት መሥዋዕት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያምጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንድ ሰው ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ ለኃጢአት መሥዋዕት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው በግሉ ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ አንድ ዓመት የሞላት እንስት ፍየል ስለ ኃጢአቱ ስርየት መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ ለኃጢአት መሥዋዕት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥
ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኀጢአት መሥዋዕት፥ ነውር የሌለበትን አውራ በግ ለደኅንነት መሥዋዕት፥
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።