ዘኍል 12:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም፥ “ሦስታችሁ ወደ ምስክሩ ድንኳን ኑ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወደ ምስክሩ ድንኳን ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያው እግዚአብሔር ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን፣ “ሦስታችሁም ውጡና ወደ መገናኛው ድንኳን ኑ” አላቸው፤ ሦስቱም ወጥተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድንገትም ጌታ ሙሴንና አሮንን ማርያምንም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ፤” ሦስቱም ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድንገትም እግዚአብሔር ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን “እናንተ ሦስታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን ኑ!” አላቸው፤ እነርሱም ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም፦ ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
እግዚአብሔርም በደመና ዐምድ ወረደ፤ በምስክሩም ድንኳን ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምንም ጠራቸው፤ ሁለቱም ወጡ።