Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መና ዐምድ ወረደ፤ በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ ቆመ፤ አሮ​ን​ንና ማር​ያ​ም​ንም ጠራ​ቸው፤ ሁለ​ቱም ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም እግዚአብሔር በደመና ዐምድ ወረደ፤ በድንኳኑም ደጃፍ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፤ ሁለቱም ወደ እርሱ በቀረቡ ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታም በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔርም በደመና ዐምድ ወርዶ በድንኳኑ ደጃፍ በመቆም “አሮን! ማርያም!” ብሎ ጠራቸው፤ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም በደመና ዓምድ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወጡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 12:5
6 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ከአ​ንተ ጋር ስነ​ጋ​ገር ሕዝቡ እን​ዲ​ሰሙ፥ ደግ​ሞም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ያ​ም​ኑ​ብህ፥ እነሆ፥ በዐ​ምደ ደመና ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ” አለው። ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ውስጥ ወረደ፤ በዚ​ያም ከእ​ርሱ ጋር ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።


ደመና በቀን በድ​ን​ኳኑ ላይ ነበ​ርና፥ እሳ​ቱም በሚ​ጓ​ዙ​በት ሁሉ በሌ​ሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በእ​ር​ስዋ ላይ ነበ​ርና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ወረደ፤ ተና​ገ​ረ​ውም፤ በእ​ር​ሱም ላይ ከነ​በ​ረው መን​ፈስ ወስዶ በሰ​ባው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ላይ አደ​ረገ፤ መን​ፈ​ሱም በላ​ያ​ቸው ባደረ ጊዜ ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ ከዚያ በኋላ ግን አል​ተ​ጨ​መ​ረ​ላ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወዲ​ያው ሙሴ​ንና አሮ​ንን ማር​ያ​ም​ንም፥ “ሦስ​ታ​ችሁ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ኑ ብሎ ተና​ገረ፤ ሦስ​ቱም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos