La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 11:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሙሴ ምርጥ ባለ​ሟል የነ​በ​ረው የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ ፥ ከል​ክ​ላ​ቸው” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ ረዳት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱም ተነሥቶ፣ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፤ ከልክላቸው እንጂ” ሲል ተናገረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ፦ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ! ከልክላቸው” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከጐልማሳነቱ ጀምሮ የሙሴ ረዳት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ! ከልክላቸው!” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ፦ ጌታዬ ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው።

Ver Capítulo



ዘኍል 11:28
9 Referencias Cruzadas  

ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ።


ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው።


ሙሴም ከኢ​ያሱ ጋር ተነሣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ራም ወጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ነ​ጋ​ገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነ​ጋ​ገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመ​ለስ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ል​ጋዩ ብላ​ቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድ​ን​ኳኑ አይ​ወ​ጣም ነበር።


አንድ ጐል​ማሳ ሰው እየ​ሮጠ መጥቶ፥ “ኤል​ዳ​ድና ሞዳድ በሰ​ፈር ትን​ቢት ይና​ገ​ራሉ” ብሎ ለሙሴ ነገ​ረው።


ወደ ዮሐ​ን​ስም ሄደው፥ “መም​ህር ሆይ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነ​በ​ረው፥ አን​ተም የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ለት እርሱ እነሆ፥ ያጠ​ም​ቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄ​ዳል” አሉት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሙ​ሴን አገ​ል​ጋይ የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦