“የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየሥርዐቱ፥ በየዓላማው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ አንጻር ይስፈሩ።
ዘኍል 1:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ሰው በየሰፈሩ፥ እያንዳንዱም ሰው በየአለቃው፥ በየጭፍራውም ይሰፍራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በየምድባቸው ድንኳናቸውን ይትከሉ፤ እያንዳንዱም ሰው በየሰፈሩና በየዐርማው ሥር ይስፈር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ በየሰፈሩ፥ በየዓላማውም፥ በየጭፍራውም ይሰፍራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎቹ እስራኤላውያን በየቡድናቸውና በየሰፈራቸው ድንኳኖቻቸውን ይተክላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ በየሰፈሩ፥ በየዓላማውም፥ በየጭፍራውም ይሰፍራሉ። |
“የእስራኤል ልጆች እያንዳንዱ በየሥርዐቱ፥ በየዓላማው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በምስክሩ ድንኳን ዙሪያ አንጻር ይስፈሩ።
የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ በየዓላማዎቻቸው ሰፈሩ፤ እንዲሁም በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተጓዙ።