ዘኍል 1:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዊን ነገድ እንዳትቈጥራቸው፥ ቍጥራቸውንም ከእስራኤል ልጆች ጋር እንዳትቀበል ዕወቅ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሌዊን ነገድ አትቍጠር፤ በእስራኤላውያንም ቈጠራ ውስጥ አታስገባው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዊን ነገድ ብቻ አትቁጠረው፥ የሕዝብ ቈጠራ ስታደርግ እነርሱን ከእስራኤል ልጆች ጋር አትቁጠር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን ወንዶችን ስትቈጥር፥ የሌዊን ነገድ አትጨምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጥራቸውንም ከእስራኤል ልጆች ጋር አታድርግ፤ |
ከአንድ ወርም ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።