ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
ዘኍል 1:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሳኮር ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳ ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የይሁዳ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ነገድ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው፥ እንደየስማቸው ቊጥር፥ ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤ ከይሁዳ ነገድ የተቈጠሩት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ |
ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
የይሁዳም ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስሮም፥ ይሞሔል፤
ኢዮአብም የሕዝቡን ቍጥር ድምር ለንጉሡ ሰጠ፤ በእስራኤልም ሰይፍ የሚመዝዙ ስምንት መቶ ሺህ ጽኑዓን ሰዎች ነበሩ፤ የይሁዳም ተዋጊዎች ሰዎች አምስት መቶ ሺህ ነበሩ።