ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የአራንን ልጅ ሎጥን፥ የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ምድር አወጣቸው። ወደ ካራንም መጡ፤ በዚያም ተቀመጡ።
ነህምያ 9:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ፤ አብራምን መረጥህ፤ ከዑር ከላውዴዎንም አወጣኸው፤ ስሙንም አብርሃም አልኸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አብራምን የመረጥኸውና ከከለዳውያን ዑር አውጥተህ አብርሃም የሚል ስም የሰጠኸው አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምን የመረጥህ፥ ከከለዳውያን ኡር የአወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም ያልኸው፥ አንተ ጌታ አምላክ ነህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ክፍል ከሆነችው ዑር፥ አብራምን መርጠህ ያመጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም ያልከው፥ አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ፥ አብራምን መረጥህ፥ ከዑር ከላውዴዎንም አወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም አልኸው፥ |
ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የአራንን ልጅ ሎጥን፥ የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ምድር አወጣቸው። ወደ ካራንም መጡ፤ በዚያም ተቀመጡ።
“ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፤ ባረክሁትም፤ ወደድሁትም፤ አበዛሁትም።
ብቻ እግዚአብሔር አባቶቻችሁን መረጣቸው፤ ወደዳቸውም፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መረጠ።