ነህምያ 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “መንግሥታትንና አሕዛብን ዕድል ፈንታ አድርገህ ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው፤ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የአሕዛብን መንግሥታትና ነገሥታትን ድል ነሥተው፥ ከምድራቸው አዋሳኞች የሆኑትን ጠረፎች እንዲይዙ አደረግህ፤ ሲሖን የተባለ ንጉሥ ይገዛት የነበረችውን ሐሴቦን ተብላ የምትጠራውን ምድር፥ በድል አድራጊነት ያዙ፤ ዖግ የተባለው ንጉሥ ይገዛት የነበረችውንም የባሳንን ምድር ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንግሥታትንና አሕዛብን ከፍለህ ሰጠሃቸው፥ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። |
ምድሪቱን፥ በምድር ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኀይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ፤ ለዐይኔም መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ።
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም፤ በሕግህም አልሄዱም፤ ያደርጉም ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
እሰጣቸውም ዘንድ እጄን ወደ አነሣሁላቸው ምድር አገባኋቸው፤ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ፥ ቅጠላማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚያም ለጣዖቶቻቸው መሥዋዕታቸውን ሠዉ፤ በዚያም የሚያስቈጣኝን፤ ቍርባናቸውን አቀረቡ፤ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ፤ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።
በሐሴቦን ተቀምጦ የነበረውን የአሞሬዎናውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስጣሮትና በኤድራይን ተቀምጦ የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከገደሉት በኋላ፥
ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመቱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞሬዎን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተ ፌጎር አቅራቢያ ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ፤
የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ፥ የዐግን ምድር፥ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱን የአሞሬዎንን ነገሥታት ምድር ወሰዱ።
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ በቤትሖሮን ቍልቍለት ሲወርዱ፥ ወደ ዓዜቃና ወደ መቄዳ እስኪደርሱ ድረስ እግዚአብሔር ከሰማይ ታላላቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸው በየነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።