ነህምያ 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕዝራም የሕዝቡ ሁሉ የበላይ ነበረና በሕዝቡ ሁሉ ፊት መጽሐፉን ገለጠ፤ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕዝራም መጽሐፉን ከፈተ፤ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ ቆሞ ስለ ነበረ፣ ሁሉም ያዩት ነበረ፣ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕዝራም ከሕዝቡ ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ ነበርና በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ፊት መጽሐፉን ከፈተ፤ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕዝራ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ በተሠራው መድረክ ላይ በቆመ ጊዜ፥ ሁሉም ትኲር ብለው ይመለከቱት ነበር፤ እርሱም የሕጉን መጽሐፍ በከፈተ ጊዜ፥ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕዝራም በሕዝቡ ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ መጽሐፉን ገለጠ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። |
በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ በወንዶችና በሴቶች በሚያስተውሉትም ፊት፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር።
ጸሓፊውም ዕዝራ ስለዚህ ነገር በተሠራ በዕንጨት መረባርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ መቲትያ፥ ሰምያ፥ ሐናንያ፤ ኦርያ፥ ሕልቅያ፥ መዕሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳኤል፥ ሚልክያ፥ ሐሱም፥ ሐስበዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላም በግራው በኩል ቆመው ነበር።
ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም።