La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ይ​ሁድ ላይ ትልቅ የሕ​ዝ​ቡና የሚ​ስ​ቶ​ቻ​ቸው ጩኸት ሆነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ወንዶቹና ሚስቶቻቸው አይሁድ ወንድሞቻቸውን በመቃወም ብርቱ ጩኸት አሰሙ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሕዝቡና የሚስቶቻቸው ጩኸት በወንድሞቻቸው በአይሁድ ላይ ትልቅ ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በአንድ ወቅት ወንዶችና ሴቶች ወገኖቻቸው በሆኑ የአይሁድ አለቆቻቸው ላይ ከባድ አቤቱታ አሰሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በወንድሞቻቸውም በአይሁድ ላይ ትልቅ የሕዝቡና የሚስቶቻቸው ጩኸት ሆነ።

Ver Capítulo



ነህምያ 5:1
15 Referencias Cruzadas  

እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።


እር​ሱም የድ​ሆ​ችን ጩኸት በእ​ነ​ርሱ ላይ ይመ​ል​ሳል፥ የች​ግ​ረ​ኞ​ች​ንም ልቅሶ ይሰ​ማል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወይን ቦታ እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ነው፤ ተወ​ዳጁ አዲስ ተክ​ልም የይ​ሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍር​ድን ያደ​ር​ጋል ብየ እጠ​ብቅ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ዐመ​ፅን አደ​ረገ፤ ጽድ​ቅ​ንም አይ​ደ​ለም፥ ጩኸ​ትን እንጂ።


ስለ አር​ነ​ታ​ቸው ዐዋጅ እን​ዲ​ነ​ግር ንጉሡ ሴዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከአ​ደ​ረገ በኋላ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው ቃል ይህ ነው።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች ሆይ! ይብ​ቃ​ችሁ፤ ግፍ​ንና ዐመ​ፅን አስ​ወ​ግዱ፤ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንም አድ​ርጉ፤ ቅሚ​ያ​ች​ሁን ከሕ​ዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህንም ደግሞ አድርጋችኋል፣ እግዚአብሔር ቍርባኑን ዳግመኛ እንዳይመለከት፥ ከእጃችሁም በደስታ እንዳይቀበለው መሠዊያውን በእንባና በልቅሶ በኅዘንም ትከድናላችሁ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊት ወደ እርሱ ለሚ​ጮኹ ለወ​ዳ​ጆቹ አይ​ፈ​ር​ድ​ምን? ወይስ ቸል ይላ​ቸ​ዋ​ልን?


በማ​ግ​ሥ​ቱም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሁለት ሰዎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲጣሉ አገኘ፤ ሊያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸ​ውም ወድዶ፦ ‘እና​ን​ተማ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናችሁ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ለምን ትጣ​ላ​ላ​ችሁ?’ አላ​ቸው።


እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፤ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ጸባዖት ጆሮ ገብቶአል።