ነህምያ 3:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የቅዔላ ግዛት እኩሌታ ገዢ የኤንሐዳድ ልጅ ቤኒይና ወንድሞቹ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ደግሞ የሌላው የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና በርሱም ሥር የነበሩት የአገሩ ሰዎች መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ ወንድሞቻቸው፥ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዚ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ አደሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የሌላው የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ ሠራው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቅዒላ ግዛት እኩሌታ አለቃ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይ ወንድሞቹም አደሱ። |
ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሁም ሠሩ። በአጠገባቸውም የቅዒላ ግዛት እኩሌታና የአውራጃዎችዋ ገዢ አሰብያ ሠራ።