ነህምያ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የአሎኤስ ልጅ ሰሎምና ሴቶች ልጆቹ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የአሎኤስ ልጅ ሰሎም ከሴት ልጆቹ ጋራ በመሆን ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም እሱና ሴት ልጆቹ የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሆነው የሃሎሔሽ ልጅ ሻሉም አደሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎ ያለውንም ክፍል የሌላው የኢየሩሳሌም ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሀሎሔሽ ልጅ ሻሉም ሠራ፤ ሴቶች ልጆቹም ሥራውን ይረዱት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታና የመንደሮችዋ አለቃ የአሎኤስ ልጅ ሰሎም አደሰ። |
በረኞቹ የሴሎምያ ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልማና ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሶባይ ልጆች መቶ አርባ ስምንት።
በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶችም በእጃቸው ፈተሉ፤ የፈተሉትንም ሰማያዊውን፥ ሐምራዊውንም፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ አመጡ።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።