እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ፥ እንድትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ!
ሚክያስ 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ ኢየሩሳሌምን በክፋት የምትገነቡ፤ ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ደም በማፍሰስ ጽዮንን፥ በደል በመሥራት ኢየሩሳሌምን የምትገነቡ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጽዮንን በደም፥ ኢየሩሳሌምንም በኃጢአት ይሠራሉ። |
እንዲህም በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጊዜሽ እንዲደርስ በመካከልሽ ደምን የምታፈስሺ፥ እንድትረክሺም በራስሽ ላይ ጣዖታትን የምታደርጊ ከተማ ሆይ!