ሚክያስ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን? “የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? እንዲህ ያሉ ነገሮችንስ ያደርጋልን?” “መንገዱ ቀና ለሆነ፣ ቃሌ መልካም አያደርግምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህ መባል አለበትን? በውኑ የጌታ መንፈስ ይቆጣልን? ሥራዎቹስ እነዚህ ናቸውን? ቃሎቼስ በቅን ለሚሄድ መልካም ነገር አያደርጉምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግራቸውንም በመቀጠል! “የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ይህ መባል አለበትን? የእግዚአብሔር ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን?” ብለው ይጠይቃሉ፤ ለመሆኑ አካሄዳቸው ቀጥተኛ ለሆነ የእኔ ቃላት መልካም ነገር አያደርጉምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን? |
እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
በኀይልህ ጩኽ፤ አትቈጥብ፤ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፤ ለሕዝቤ ኀጢአታቸውን፥ ለያዕቆብ ቤትም በደላቸውን ንገር።
ቃልህ ተገኝቶአል፤ እኔም በልችዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቃልህን የከዱ ሰዎችን አጥፋቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠርትዋልና፥ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአሔርም ሙሴን፥ “በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አትችልምን? አሁን ቃሌ ይፈጸም ወይም አይፈጸም እንደ ሆነ እነሆ፥ አንተ ታያለህ” አለው።
እነርሱም መልሰው፥ “የእኛስ አባታችን አብርሃም ነው” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የአብርሃም ልጆች ብትሆኑስ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር።
እንግዲህ ያ መልካም ነው ብዬ የማስበው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላለሁን? አይደለም፤ ነገር ግን ኀጢአት ኀጢአት እንደ ሆነች በታወቀች ጊዜ ሞትን አበዛችብኝ፤ ከዚያም ትእዛዝ የተነሣ ኀጢአተናው እንዲታወቅ፥ ኀጢአትም ተለይታ እንድትታወቅ ኦሪት መልካሙን ከክፉ ልትለይ ተሠርታለች።