ማቴዎስ 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያው ይሆናልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይሆናልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። |
በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።
እነሆ ዐይንህና ልብህ መልካም አይደለም፤ ነገር ግን ለቅሚያ፥ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ፥ ግድያንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ተስፋ አናደርግም፤ የሚታየው ኀላፊ ነውና፥ የማይታየው ግን ለዘለዓለም የሚኖር ነው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ዕወቁ፤ ከእናንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይማኖት የጐደለውና ተጠራጣሪ፥ ከሕያው እግዚአብሔር የሚለያችሁ ክፉ ልብ አይኑር።