በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
ማቴዎስ 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤መፅናናትን ያገኛሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መጽናናትን ያገኛሉና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤ መፅናናትን ያገኛሉና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር መጽናናትን ስለሚሰጣቸው የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና። |
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
ሞት ሰዎችን ዋጠ፤ በረታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር በአፉ ተናግሮአልና።
ቅዱስ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን ይኖራል፤ ልቅሶን አልቅሺ፤ ይቅር በለኝም በዪ፤ ልቅሶሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይልሻል፤ ሰምቶሻልና።
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
ኢየሩሳሌም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ እርስዋንም የምትወድዱአት ሁሉ፥ በአንድነት ሐሤት አድርጉ፤ ስለ እርስዋም ያለቀሳችሁ ሁሉ፥ ከእርስዋ ጋር ደስ ይበላችሁ፤
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ፤ መብረርን እንደሚማር ርግብም በተራራ ላይ ይሆናሉ፤ እኔም በኀጢአታቸው ሁሉ እገድላለሁ።
እግዚአብሔርም፥ “በከተማዪቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ኀጢአት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።
ዛሬ ለምትጠግቡ፥ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና፤ ዛሬ ለምትስቁም ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና፤ ታለቅሳላችሁምና።
በስተኋላውም በእግሮቹ አጠገብ ቆማ አለቀሰች፤ እግሮቹንም በእንባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕርዋም እግሮቹን ታብሰውና ትስመው፥ ሽቱም ትቀባው ነበር።
እንባዎችንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ ሐዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፤ የቀደመው ሥርዐት አልፎአልና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።