እርስዋ ይህን ሽቱ በሰውነቴ ላይ አፍስሳ ለመቃብሬ አደረገች።
ሽቱውን በሰውነቴ ላይ ማፍሰሷ፣ እኔን ለቀብር ለማዘጋጀት ነው፤
እርሷ ይህን ሽቶ በሰውነቴ ላይ በማፍሰስ ለቀብሬ አደረገችው።
እርስዋ ይህን ሽቶ በእኔ ላይ ማፍሰስዋ እኔን ለቀብር ለማዘጋጀት ነው።
ዮሴፍም ባለ መድኀኒቶች አገልጋዮቹ አባቱን በሽቱ ያሹት ዘንድ አዘዘ፤ ባለ መድኀኒቶችም እስራኤልን በሽቱ አሹት።
ለእርሱም ለራሱ በሠራው መቃብር በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ በቀማሚ ብልሃት የተሰናዳ ልዩ ልዩ መልካም ሽቱ በተሞላ አልጋ ላይም አኖሩት፤ እጅግም ታላቅ የሆነ የቀብር ሥርዐት አደረጉለት።
የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው።
ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቶ ገዙ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለ፥ “ለምቀበርበት ቀን ትጠብቀው ዘንድ ተዉአት።