እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ማቴዎስ 18:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሒሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺሕ ታላንት ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መተሳሰብ በጀመረ ጊዜ፥ አስር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ መተሳሰብ በጀመረ ጊዜ በብዙ ሺህ መክሊት የሚቈጠር ዕዳ ያለበት አንድ አገልጋይ ተይዞ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቍኦጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። |
እርሱም አለ፥ “አሁንም እንዲሁ እንደ ነገራችሁ ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት እርሱ ለእኔ አገልጋይ ይሁነኝ፤ እናንተም ንጹሓን ትሆናላችሁ።”
ለእግዚአብሔርም ቤት ሥራ አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክሊት ብር፥ ዐሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።
እንዲህም አልሁ፥ “አምላኬ ሆይ፥ ኀጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቶአልና፥ በደላችንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎአልና አምላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍራለሁ፤ እፈራማለሁ።
አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ ‘ጌታ ሆይ! አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት፤’ አለ።
ወይስ እነዚያ በሰሊሆም ግንብ ተጭኖ የገደላቸው ዐሥራ ስምንቱ ሰዎች ከኢየሩሳሌም ሰዎች ይልቅ ተለይተው ኀጢእታኞች ይመስሉአችኋልን?
ለጌታውም ዕዳ የሚከፍሉትን ጠራቸው፤ የመጀመሪያውንም፦ ‘ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ዘይት ነው’ አለው።
ሁለተኛውንም፦ ‘አንተሳ ለጌታዬ የምትከፍለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እርሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብዳቤህ፤ ተቀምጠህ ሰማንያ አለብኝ ብለህ ፈጥነህ ጻፍ’ አለው።