አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ።
ማቴዎስ 14:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታንኳይቱም አሁን በባሕር መካከል ሳለች፥ ነፋስ ከወደ ፊት ነበርና በማዕበል ትጨነቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ጀልባዋ ከምድር ብዙ ምዕራፍ ርቃ እየተጓዘች ሳለች ነፋስ ተነሥቶ በማዕበል ትንገላታ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ጀልባዋ ከምድር በጣም ርቃ ሳለች፥ ነፋስ በተቃራኒው አቅጣጫ ነበርና በማዕበል ትንገላታ ጀመር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ጀልባዋ በባሕሩ መካከል ሆና ከምትሄድበት አቅጣጫ በተቃራኒ በሚነፍሰው ነፋስ እየተመታች ማዕበሉ ወዲያና ወዲህ ያንገላታት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታንኳይቱም አሁን በባሕር መካከል ሳለች፥ ነፋስ ከወደ ፊት ነበርና በማዕበል ትጨነቅ ነበር። |
አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ።
ነፋስ ከወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሄደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር።