ማርቆስ 9:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኀ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እላችኋለሁ፣ የክርስቶስ በመሆናችሁ በስሜ አንድ ኩባያ ውሃ የሚሰጣችሁ ሁሉ ዋጋውን አያጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እላችኋለሁ፥ የክርስቶስ በመሆናችሁ በስሜ አንድ ኩባያ ውሃ የሚሰጣችሁ ሁሉ ዋጋውን አያጣም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እላችኋለሁ፤ የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ አንድ ብርጭቆ ውሃ እንኳ የሚያጠጣቸው ዋጋውን አያጣም፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ። |
በመብል ምክንያት ባልንጀራህን የምታሳዝን ከሆንህ ፍቅር የለህም፤ በውኑ ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለት ያ ሰው በመብል ምክንያት ሊጐዳ ይገባልን?
እናንተ ግን ለመንፈሳዊ ሕግ እንጂ ለሥጋችሁ ፈቃድ የምትሠሩ አይደላችሁም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ አድሮ ይኖራልና፤ የክርስቶስ መንፈስ ያላደረበት ግን እርሱ የእርሱ ወገን አይደለም።
ነገር ግን ሰው ሁሉ በየሥርዐቱ ይነሣል፤ በመጀመሪያ ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ያመኑ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ይነሣሉ።
በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ፤ ማንም በክርስቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛም እንዲሁ ነንና።