እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”
ማርቆስ 8:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ ነህ፤” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ ነህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጥሎም፥ “እናንተሳ ማን ትሉኛላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፤ “አንተ ክርስቶስ ነህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፦ “አንተ መሲሕ ነህ፤” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም፦ አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት። |
እንዲህም አላቸው “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን፥ ‘አይተው እንዲያዩ እንዳይመለከቱም፤ ሰምተውም እንዲሰሙ እንዳያስተውሉም፤ እንዳይመለሱ ኀጢአታቸውም እንዳይሰረይላቸው’ ነገር ሁሉ በምሳሌ ይሆንባቸዋል።”
እርስዋም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ” አለችው።
ሴቲቱንም፥ “እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለም መድኀኒት ክርስቶስ እንደ ሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ በአንቺ ቃል ያመንበት አይደለም” አሏት።