ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
ማርቆስ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ “ሁላችሁ እኔን ስሙ፤ አስተውሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙኝ፤ ሁላችሁም አስተውሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙኝ፤ ሁላችሁም አስተውሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡንም እንደገና ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ሁላችሁም በማስተዋል አዳምጡኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ፦ ሁላችሁ እኔን ስሙ አስተውሉም። |
ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
ሚክያስም፥ “በሰላም ብትመለስ እግዚአብሔር በእኔ የተናገረ አይደለም” አለ። ደግሞም አሕዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።
እርሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፥ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ፥ አትመለከቱምም” በላቸው አለኝ።
በዚያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ ይላቸው ጀመረ፥ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፤ ይኸውም ግብዝነት ነው።
ፊልጶስም ፈጥኖ ደርሶ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማው፤ ፊልጶስም፥ “በውኑ የምታነበውን ታውቀዋለህን?” አለው።