ሁሉም እያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ደጋግመውም ገደሉ። ከዚህም በኋላ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴርም በፈጣን ፈረስ አመለጠ።
ማርቆስ 6:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው መሆኑን ሄሮድስ በማወቁ ይፈራውና ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ሄሮድስ ቢታወክም በደስታ ያደምጠው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው መሆኑን ሄሮድስ በማወቁ ይፈራውና ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ሄሮድስ ቢታወክም በደስታ ያዳምጠው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄሮድስ በመጀመሪያ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ መሆኑን ስለሚያውቅ ይፈራውና ይጠብቀውም ነበር። ሄሮድስ የዮሐንስን ንግግር በሰማ ቊጥር ይታወክ ነበር፤ ይሁን እንጂ በደስታ ይሰማው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ |
ሁሉም እያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ደጋግመውም ገደሉ። ከዚህም በኋላ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴርም በፈጣን ፈረስ አመለጠ።
ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላቸውና ፈረሰኛቸው” አለ።
እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ፤ በዘመኑም እግዚአብሔርን ፈለገ፤ እግዚአብሔርም ነገሩን አከናወነለት።
እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠ፤ አዋሱአቸውም፤ ይህ ሙሴም በግብፃውያንና በፈርዖን፥ በሹሞቹም ፊት እጅግ የከበረ ሰው ነበረ።
እነሆ አንተ መልካም ድምፅ እንዳለው እንደሚወደድ መዝሙር ማለፊያም አድርጎ በገና እንደሚጫወት ሰው ሁነህላቸዋል፤ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም።