ከሰማይ ተመለስ፤ ከቅድስናህና ከክብርህ ማደሪያም ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህስ ወዴት ነው? የቸርነትህና የይቅርታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለሃልና።
ማርቆስ 4:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ግን ትራስ ተንተርሶ ከጀልባዋ በስተኋላ በኩል ተኝቶ ነበር። እነርሱም ቀስቅሰውት፣ “መምህር ሆይ፤ ስንጠፋ አይገድድህምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ቀስቅሰውትም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ኢየሱስ፥ በጀልባው በኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ቀሰቀሱትና “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ አንቅተውም፦ መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት። |
ከሰማይ ተመለስ፤ ከቅድስናህና ከክብርህ ማደሪያም ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህስ ወዴት ነው? የቸርነትህና የይቅርታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለሃልና።
ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤
ቀርበውም፥ “መምህር ሆይ፥ መምህር ሆይ፥ ልንጠፋ ነው” ብለው ቀሰቀሱት፤ ተነሥቶም ነፋሱንና የውኃዉን ማዕበል ገሠጻቸው፤ እነርሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥታም ሆነ።
በዚያም የያዕቆብ የውኃ ጕድጓድ ነበረ። ጌታችን ኢየሱስም መንገድ በመሄድ ደክሞ በዚያ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበር።
ስለዚህም የሕዝብን ኀጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።