እግዚአብሔርም ሰይጣንን፥ “እነሆ፥ ለእርሱ ያለውን ሁሉ በእጅህ ሰጠሁህ፥ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ።
ማርቆስ 4:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ተነሣ፤ ማዕበሉም ውሃ እስኪሞላት ድረስ ጀልባዋን ያናውጣት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ውሃው በጀልባው እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ ጀልባውን ይመታ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። |
እግዚአብሔርም ሰይጣንን፥ “እነሆ፥ ለእርሱ ያለውን ሁሉ በእጅህ ሰጠሁህ፥ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ።
እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ ድንገት መጥቶ ቤቱን በአራት ማዕዘኑ መታው፥ ቤቱም በብላቴኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።”
እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፤ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፤ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
መርከቢቱም በሁለት ታላላቅ ድንጋዮች መካከል ተቀረቀረች፤ ባሕሩም ጥልቅ ነበረ። ከወደፊቷም ተያዘች፤ አልተንቀሳቀሰችምም፤ ከሞገዱም የተነሣ በስተኋላ በኩል ጎንዋን ተሰብራ ተጐረደች፤ ቀዛፊዎችም ወደፊት ሊገፉአት አልቻሉም።
ሦስት ጊዜ በበትር ደበደቡኝ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ መቱኝ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረች፤ በጥልቁ ባሕር ውስጥ ስዋኝ አድሬ፥ ስዋኝ ዋልሁ።