ሐዋርያት ሥራ 27:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 መርከቢቱም በሁለት ታላላቅ ድንጋዮች መካከል ተቀረቀረች፤ ባሕሩም ጥልቅ ነበረ። ከወደፊቷም ተያዘች፤ አልተንቀሳቀሰችምም፤ ከሞገዱም የተነሣ በስተኋላ በኩል ጎንዋን ተሰብራ ተጐረደች፤ ቀዛፊዎችም ወደፊት ሊገፉአት አልቻሉም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም41 ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቍልል ጋራ ተላትሞ መሬት ነካ፤ የፊተኛው ክፍሉም አሸዋው ውስጥ ተቀርቅሮ አልነቃነቅ አለ፤ የኋለኛው ክፍሉም በማዕበሉ ክፉኛ ስለ ተመታ ይሰባበር ጀመር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 ነገር ግን ሁለት ባሕር በተገናኙበት ስፍራ ወድቀው መርከቡን በዲብ ላይ ነዱ፤ በስተ ፊቱም ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተ ኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊያ የተነሣ ይሰበር ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቊልል ጋር በመጋጨቱ ቊልቊል ተደፋ፤ በስተፊቱም ወደ ታች ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊት የተነሣ ይሰባበር ጀመር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 ነገር ግን ሁለት ባሕር በተገናኙበት ስፍራ ወድቀው መርከቡን በዲብ ላይ ነዱ፤ በስተ ፊቱም ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፥ በስተ ኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊያ የተነሣ ይሰበር ነበር። Ver Capítulo |