ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ማርቆስ 4:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንድ ሰዎች በመንገድ ላይ የወደቀውን ዘር ይመስላሉ፤ ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ ሰይጣን ወዲያውኑ መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የነበሩት፦ እነርሱ በሰሙት ጊዜ ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸው ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሉ በተዘራ ጊዜ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል የሚወስድባቸውን ሰዎች ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል። |
ሎጥም ወጣ፤ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም አላቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋታልና።” ለአማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ጴጥሮስም፥ “ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልለው ዘንድ፥ የመሬትህንም ዋጋ ከፍለህ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ እንዴት አደረ?
ይድኑ ዘንድ የእውነት ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዐመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።
ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።