ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
ማርቆስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽባውን ‘ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤’ ከማለት ወይስ ‘ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ፤’ ከማለት ማናቸው ይቀላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽባውን፣ ‘ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል’ ከማለትና፣ ‘ተነሥተህ ዐልጋህን ተሸክመህ ሂድ’ ከማለት የቱ ይቀልላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽባውን ‘ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል፤’ ከማለትና ‘ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ፤’ ከማለት የቱ ይቀላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽባውን፥ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል፤’ ከማለትና፥ ‘ተነሥተህ አልጋህን ተሸከምና ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽባውን፦ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣ አልጋህንም ተሸከምና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? |
ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
እነሆም፥ በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን “አንተ ልጅ! አይዞህ፤ ኀጢአትህ ተሰረየችልህ፤” አለው።