ማርቆስ 16:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ማለዳ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት በመጀመሪያ ታየ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ማለዳ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፥ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለማርያም መግደላዊት በመጀመሪያ ታየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን (እሑድ) በማለዳ ከሞት ከተነሣ በኋላ፥ መጀመሪያ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ። |
ሴቶችም ደግሞ በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም በገሊላ ሳለ ይከተሉትና ያገለግሉት የነበሩ መግደላዊት ማርያም የታናሹ ያዕቆብና የዮሳም እናት ማርያም ሰሎሜም ነበሩ፤
መንቀጥቀጥና መደንገጥ ይዞአቸው ነበርና ወጥተው ከመቃብር ሸሹ፤ ይፈሩ ነበርና ለማንም አንዳች አልነገሩም። እነርሱም ያዘዛቸውን ሁሉ ለጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ላሉት በአጭሩ ተናገሩ። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።
እነዚያም መግደላዊት ማርያም፥ ዮሐና፥ የያዕቆብ እናት ማርያም፥ አብረዋቸው የነበሩት ባልንጀሮቻቸውም ይህን ለሐዋርያት ነገሩአቸው።
ከክፉዎች አጋንንትና ከደዌያቸው ያዳናቸው ሴቶችም አብረውት ነበሩ። እነርሱም፦ መግደላዊት የምትባለው ሰባት አጋንንት የወጡላት ማርያም፥
ሁለት መላእክትንም ነጭ ልብስ ለብሰው የጌታችን የኢየሱስ ሥጋ በነበረበት ቦታ አንዱ በራስጌ፥ አንዱም በግርጌ ተቀምጠው አየች።
ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን እሑድ ማዕድ ለመባረክ ተሰብስበን ሳለን ጳውሎስ በማግሥቱ የሚሄድ ነውና ያስተምራቸው ጀመረ፤ እስከ መንፈቀ ሌሊትም ድረስ ትምህርቱን አስረዘመ።
እኔ ስመጣ ይህ የገንዘብ ማዋጣት ያንጊዜ እንዳይሆን፥ ከእናንተ ሰው ሁሉ በየሳምንቱ እሑድ የተቻለውን ያወጣጣ፤ ያገኘውንም በቤቱ ይጠብቅ።